ቻት ጂፒቲ እስከዛሬ ካሉት Artificial Intelligence (ሰው ሰራሽ አስተውሎት ) በተሻለ ሁኔታ ለጥያቄዎ ፈጣን መረጃን በማቀበል ይታወቃል ቻት ጂፒቲ አገልግሎት ላይ የዋለው በ ህዳር ወር ሲሆን አገልግሎት ላይ በዋለም በ 1 ሳምንት ውስጥ ከ 1 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎችን አጊኝቷል ሲል የቻት ጂፒቲ ባለቤት የሆነው Open AI ተናግሯል
ቻት ጂፒቲን ለመጠቀም ኣካውንት መክፈት የሚያስፈሊግ ሲሆን ከዚያም በሗላ ለሚጠይቁት ነገር ሁሉ አለም ያላትን መረጃ በማሰስ እንደ ጥያቄው አይነት ምላሽ ይሰጣል የሚሰጠው ምላሽም አጅግ የተዋጣ ነው፡፡
ይህ ሶፍትዌር የተጠየቀውን ይመልሳል፤ የጥናት ጽሁፍ ያጠናቅራል፤ ፈተና ያለ አንዳች ችግር ይመልሳል እንዲሁም ሌሎች የጽሁፍ ስራዎችን ያለችግር ይሰራል። ቻት ጂፒቲ አንዴ ከተሰራ በኋላ ያለ ሰው ልጅ ተጽዕኖ ራሱን በራሱ የሚያስተዳድርና የሚያስተምር ቴክኖሎጂ ሲሆን በሂደትም ኢንተርኔት ላይ ያለውን እውቀት በሙሉ በማግበስበስ የሚሰራ ራስ-አገዝ ቴክኖሎጂ ነው።
በልላ በኩል ደሞ ተማሪዎች የተሰጣቸውን የቤት ስራ ወደ ቻት ጂፒቲ በማስገባት የጥያቄዎቻቸው መልስ በማግኘት እራሳቸው እንደሰሩ አድረገው ያቀርባሉ ይህንንም ለማስቀረት በነዚህ በ Artificial Intelligence የተፃፉ ፅሁፎችን የሚለዩ ልሎቸ የ Artificial Intelligence ውጤቶቸ እየተሰሩ ነው
የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ውስጥ የሚካተቱት እንደ ቻት ጂፒቲ ያሉት መተግበሪያዎች የተማሩ ሰዎች የሚሰሯቸውን ሥራዎች ሊተኩ የሚችሉ መሆናቸው ይበልጥ ስጋት አንብሯል፡፡
የትዊተር ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢሎን መስክንና የዘርፉ ምሁራን እንደ ቻት ጂፒቲ ያሉ የሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂዎች ላይ የ6 ወራት እገዳ እንዲጣል መጠየቃቸው ተነግሯል፡፡
ምንጭ ፤-ሲጂቲኤን ፤ ፒሲ ጋይድ ፤ ኦፕን ኤ አይ