የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ጥናትና ምርምር አውደ ጥናት ተካሄደ፡፡

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ጥናትና ምርምር አውደ ጥናት ተካሄደ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተዘጋጀ የጥናትና ምርምር አውደጥናት በዛሬው እለት በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል ተካሄዷል፡፡ በመድረኩም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ዋና ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ የመግቢያ ንግግር አድርገዋል፡፡ከሠኔ 1-3 2015ዓ.ም የሚቆይ ከተማ አቀፍ የፈጠራ ስራ ውድድር አውደርዕይ የተከፈተ ሲሆን በዚህም የተለያዩ የፈጠራ ስራዎች እየቀረቡ እንደሚገኙና በዛሬው ዕለትም ልዩ ሁኔታ የተማሪዎችን ባህሪያት እና የመማር ማስተማሩን ሂደት ያሻሽላሉ ተብለው የታሰቡ ሁለት መሰረታዊ ጥናቶች በመድረኩ ተነስተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ይን ጥናት ተቀብሎ አስተያየት እና ግምገማ ካደረገበት ቡሃላም ወደስራ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ አሊ ከማል ተናግረዋል፡፡ የቀረቡት የጥናትና ምርምሮች በአዘጋጆቹ በቂ ማብራሪያ የተደረገባቸው ሲሆን ሁለቱም ጥናቶች አሁን ላይ በተማሪዎቹ ላይ የሚታዩ ተጨባጭ ችግሮችን የዳሰሰ እና ተገቢ መፍትሄ እንደሚያስፈልገው እንዲሁም ይህ ጥናት በየአመቱ ሊሰራ የሚገባ ትኩረት የሚሻ መሰረታዊ ሃሳብ እንደሆነ በመድረኩ ተገልጧል፡፡ በጥናቱም ላይ የተለያዩ መምህራን እንዲሁም የተማሪ ወላጆች ጥያቄና አስተያየታቸውን አንስተውበታል፡፡

Leave a Reply