8ኛው ከተማ አቀፍ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራ ዐውደ ርእይ ተጠናቀቀ።
“በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ የዳበረ ትውልድ ለሀገር ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል ከሰኔ1 ጀምሮ ለተከታታይ 3 ቀናት ሲካሄድ የነበረው ከተማ አቀፍ አውደርእይ ዛሬ በወዳጅነት አደባባይ የተለያዩ ደማቅ መርሃ ግብሮች ተሰንደውበት ተካሂዷል።
የመክፈቻ ንግግሩን ያደረጉት የአዲስ አበባ ት/ቢሮ ም/ሀላፊ በሳይንስና ቴክኖሎጂ አውደርእዪ ላይ 11 ክፍለ ከተሞች እና 2 አዳሪ ት/ቤቶችን የወከሉ ተወዳዳሪዎች እንደተሳተፉበት ገልፀዋል።
ውድድሩ በ1ኛ ደረጃ በሁለት ስርዓተ ትምህርቶች ማለትም በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ፤ በሂሳብ ፣ በአካባቢ ሳይንስ እና በአጠቃላይ ሳይንስ የተካሄደ ሲሆን የውድድሩ ተሳታፊዎችም መምህራን እና ተማሪዎች ናቸው።
በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ተወዳድረው በአንደኝነት ውድድሩን አሸንፈው የተመረጡ ሲሆኑ በ5ቱ ዘፎች በሂሳብ ፣ በኬሚስትሪ ፣ በፊዚክስ ፣ በባዮሎጂ እንዲሁም በICT የትምህርት ዘርፎች ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን ውድድሩ በልዩ ፋላጎት የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችንም እንዳካተተ ተመልክቷል።
በፋፃሜው ውድድር በአጠቃላይ ፈጠራ ውጤት ለሚኩራ ክ/ከተማ አሸናፊ ሲሆን በሽብርቅ ጭፈራ ደግሞ ጉለሌ ክ/ከተማ የመጀመሪያው አሸናፊ ሲሆን አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሁለተኝነቱን ይዞ ቦሌ ክ/ከተማ ደግሞ ሦሥተኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቋል።