ለ 3 ቀናት የሚቆየው የነጋዴ ሴቶች ኤክስፖ 2015 በስካይላይት ሆቴል በይፋ ተከፈተ፡፡
የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከማሌሳ ኤቨንትስ ጋር በጋራ በመሆን ያዘጋጁት business women expo 2023 በትላንትናው ዕለት የመንግስት ባለስልጣናት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በይፋ ተከፍቷል፡፡ የሴቶች እና የማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በኤክስፖው በመገኘት የሪቫን መቁረጥ ስነስርዓት በማድረግ የኤክስፖውን በይፋ መጀመር አስታውቀዋል፡፡ ከመክፈቻዉም ቡሀላ ምርቶቻቸዉን እየተዘዋወሩ በመጎብኘት አበርትተዋቸዋል። በመክፈቻው ላይም የማሌሳ ኤቨንትስ ዋና ስራ አስኪያጅ ሰላማዊት ደጀን እንደተናገረችው ይህን ኤክስፖ ለማዘጋጀት በብዙ ውጣውረዶች እንዳለፈችና በመጨረሻም በመሳካቱ የተሰማትን ደስታ እና የእንኳን ደስ አላቹ መልዕክት አስተላልፋለች፡፡ ኤክስፖው ከሰኔ 7-9 2015ዓ.ም ሚቆይ ሲሆን በዋነኝነት ሴት ስራ ፈጣሪዎችን እንዲሁም አምራቾችን ለማበረታታት፣ ከሌሎች ተቋማት ጋር መገናኘት እንዲችሉ እና ለወደፊትም የስራ ዕድሎችን የሚከፍት ነው ተብሏል፡፡ ኤክስፖው ከ100በላይ ድርጅቶች እና ከ 40ሺ በላይ ጎብኚዎች ይሳተፉበታል የተባለ ሲሆን ሴት አምራቾችም ምርቶቻቸውን ለገዢዎች የሚያቀርቡበት እና የተለያዩ ልምድ እና ተሞክሮዎችንም የሚለዋወጡበት እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ ለወደፊቱም ኤክስፖው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ይህ ጅማሮ እንደሆነም በመክፈቻ ስነስርዓቱ ተጠቅሷል፡፡
በመቅደላዊት ዘዉዱ